“ከናይሮቢ – አዲስ አበባ በአውቶብስ የሕዝብ ትራንስፖርት እንደተጀመረ ” አላውቅም አለ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

ቢቢሲ አማርኛ “ከናይሮቢ – አዲስ አበባ በአውቶብስ የሕዝብ ትራንስፖርት ተጀመረ” በሚል ያሰራጨው ዘገባ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ እውቅና ውጪ ነው ሲል የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል ።

ቢቢሲ አማርኛ በድረገጹ “አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች’ የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን አስታወቀ” ሲል መዘገቡን ያስታወሰው ሚኒስትሩ ይህ ነገር ከእኔ እውቅና ውጪ ነው፡፡እኔም አልተጠየኩበትም ብሏል፡፡

ሆኖም ይህንን ጉዳይ በሀገሪቱ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ላይ በአዋጅ ሀላፊነት የተሰጠው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የማያውቀው መሆኑን ገልጻል ።

እንደሀገር በ 2018 በጀት አመት በሁለቱ ሀገራት መካከል ትስስር ለመፍጠር ይህንን አገልግሎት ለመጀመር እቅድ የተያዘ ቢሆንም ሂደቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል የትብብር ስምምነት መፈራረም፣ ታሪፍ በጋራ መወሰን እና ሌሎች የዲፒሎማሲ ጉዳዮች የሚፈልግ በመሆኑ ከሚመለከተው መንግስታዊ መስሪያቤት ጋር በመተባበር የሚሰራበት መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል ።

ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *