የፑቲን – ትራምፕ ስብሰባ የዘለንስኪ ቅድመ ሁኔታ እንደሌለው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ በፑቲን እና በዘለንስኪ መካከል በሚደረግ ግንኙነት ላይ የተመሠረተ አይደለም ብለዋል።

ትላንት የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ከሦሶት ዓመት በላይ የዘለቀው የዩክሬን ጦርነት በሚያበቃበት መንገድ ላይ ለመወያየት ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገረው ነበር፡፡

የፑቲን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ ትላንት ፣ ምንም እንኳን መሰል ንግግሮችን ለማዘጋጀት ጊዜ ቢወስድም ውይይቱ በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሊካሄድ ይችላል ብለዋል።

ጉባኤው በትክልል መቼ እንደሚካሄድና የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ በጉባኤው ላይ ስለ መሳተፍ አለመሳተፋቸው ግን አልተናገሩም ።

አንድ በይፋ ለመናገር ያልተፈቀደላቸው የዋይት ሀውስ ባለሥልጣን እንደተናገሩት የጉባኤው ቦታም አልተወሰነም እንደ ስፑትኒክ ዘገባ።

ነሐሴ 2/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *