የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ጋር የነበረውን የንግድ እገዳ ለተጨማሪ 90 ቀናት አራዘሙ

ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ፕላትፎርማቸው ላይ የእገዳውን ማራዘሚያ የሚያዝዘውን የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ መፈረማቸውን የገለፁ ሲሆን “የስምምነቱ ሌሎች አካላት በሙሉ እንደነበሩ ይቀጥላሉ” ብለዋል። የቻይና ንግድ ሚኒስቴር በበ
ኩሉ ቀረጥ የማቆም ውሳኔው መራዘሙን በተመሳሳይ ጊዜ አስታውቋል።

ማስታወቂያው ከዚህ ቀደም የተሰጠው ጊዜ ከማብቃቱ ጥቂት ሰዓታት በፊት ነው የወጣው።

ይህ ባይሆን ኖሮ ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ምርቶች ላይ ቀድሞውንም ከፍ ያለውን 30% ቀረጥ ልታሳድግ ትችል ነበር፣ ቻይናም በበኩሏ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች ላይ አፀፋዊ ቀረጥ በመጨመር ምላሽ ልትሰጥ ትችል ነበር ተብሏል።

ይህ እረፍት ሁለቱ ሀገራት ልዩነቶቻቸውን እንዲፈቱ ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ምናልባትም በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ መካከል ለሚደረግ ጉባኤ መንገድ ሊከፍት ይችላል።

ትራምፕ ሚያዝያ ወር ላይ ቀረጥ መጣል ከጀመሩ በኋላ ቻይና ለአንዳንድ የአሜሪካ ኩባንያዎች የሚውሉ ድርብ ጥቅም ያላቸውን እቃዎች ወደ ውጭ መላክን የገደበች ሲሆን ሌሎችን ደግሞ ወደ ቻይና እንዳይገቡ ወይም ኢንቨስት እንዳያደርጉ ከልክላለች።

በግንቦት ወር በጄኔቫ በተደረገ ስብሰባ ወደ ኋላ ለማፈግፈግ እና መነጋገራቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል፡ የአሜሪካ ቀረጥ ወደ 30 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን የቻይና ደግሞ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ብሏል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ድርድሮች ቀጥለዋል ሲል የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው።

ሀኒፍ ሀምዛ

ነሐሴ 7/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *