የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ቪንሴንት ማግዌንያ “ሩሲያ እና የአሜሪካ መሪዎች መካከል በአንኮሬጅ የሚደረገው መጪው ውይይት የዩክሬን ቀውስ እልባት መስጫ መንገዶችን ለመፈለግ ወሳኝ ሁነት ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ የአላስካ ስብሰባ ሁሉንም ባለድርሻ ባሳተፈ መልኩ የዩክሬን ድርድር ለማፋጠን መንገድ ይከፍታል ብላ ተስፋ ታደርጋለች” ሲሉ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል።
ባለፈው ሳምንት ከፑቲን እና ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ያደረጉት ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ ስለተጠባቂው የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ በቂ ግንዛቤ እንዳላቸውም አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
ፑቲን እና ትራምፕ ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ገደማ በአላስካ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ትራምፕ በአላስካ ከፑቲን ጋር ለሚያደርጉት ስብሰባ በኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን ጉዞ ጀምረዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕን የሚያጅቡ ተሽከርካሪዎች ፕሬዝዳንቱ ወደ አላስካ ማምራታቸውን ተከትሎ ወደ ጆይንት ቤዝ አንድሪውስ አውሮፕላን ማረፊያ አቅንተዋል እንደ ስፑትኒክ ዘገባ።
ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም
