ሶማሊያ በአልሸባብ ላይ ባካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውን አስታወቀች

የደህንነት ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፤የዳናብ ልዩ ኃይል ወታደሮች በታችኛው ሸበሌ ክልል በሚባል ቦታ ውስጥ በሚገኙ የአልሸባብ መደበቂያዎች ላይ ወረራ እንደፈጸሙ ገልጸዋል፡፡

ውጊያው እሁድ ምሽት የጀመረ ሲሆን፤ እስከ ሰኞ ማለዳ ድረስ እንደቀጠለ እና ታጣቂዎቹ ባሉበት ቦታዎች ላይ የአየር ድብደባ ጥቃት ጭምር ተፈጽሟል ተብሏል፡፡

ከሐምሌ ወር ጀምሮ የሶማሊያ ኃይሎች እና የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪዎች በአገሪቱ መሃል እና በደቡብ አካባቢ በሚገኙ የአልሸባብ ምሽጎች ላይ ዘመቻቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

ታጣቂዎቹ ሞቃዲሾን ጨምሮ በከተማ አካባቢዎች ላይ ጥቃት ስለሚሰነዝሩ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ፤ አልሸባብን ማሸነፍ የእቅዳቸው ዋነኛ አካል ያደረጉ ቢሆንም አንዳንድ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች መውጣታቸውን ተከትሎ በሶማሊያ ወታደሮች ውስጥ ክፍተቶች መፈጠራቸውን አስታዉቀዋል፡፡

አል-ሸባብ ከ16 ዓመታት በላይ በሶማሊያ መንግስት ላይ አመጽ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡

የጸጥታ ኃይሎችን፣ የመንግስት ባለስልጣናትን እና ንጹሃን ዜጎችን ኢላማ እያደረገ መቆየቱን አናዶሉ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ኤርሚያስ ገረመዉ

ነሐሴ 13/ 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *