በተለያዩ መንገዶች ተፅዕኖ የሚፈጥሩ የዲያስፖራ አካላትን በአጀንዳ ማሰባሰቡ ላይ እንዲሳተፉ በደብዳቤ ጠይቄያለሁ ሲል የምክክር ኮሚሽኑ ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሰሜን አሜሪካና በካናዳ የሚካሄዱ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተወካዮች ምርጫ ተግባራትን ለማከናወን ቅድመ ዝግጅቶች እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሂደቱም በቀጣይ ሳምንታት እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

በፖለቲካ አቋማቸው የሚታወቁ የዲያስፖራው ማህበረሰብ ተቋማት፣ ማህበራትና ግለሰቦች ጭምር እንዲሳተፉ ስማቸው ተጠቅሶ በደብዳቤ ተጠይቀዋል ያሉት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ናቸው፡፡

ቃል አቀባዩ ለብዙሃን መገናኛዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሰሜን አሜሪካና በካናዳ፣ እንዲሁም በሌሎች ሀገራት አጀንዳ ማሰባሰብ ያስፈለገው የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወገኖችን ለማሳተፍ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ኮሚሽኑ ባዘጋጃቸውየመመዝገቢያ አማራጮች እንዲመዘገቡና እንዲሳተፉ ሁኔታዎች ይመቻቻሉ ብለዋል፡፡ እንደኮሚሽኑ ገለፃ ምዝገባው ያስፈለገው የመሰብሰቢያ ቦታዎችንና ሌሎች የሎጅስቲክ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነው፡፡

መድረኩን በማመቻቸት የበኩሌን ድርሻ እየተወጣሁ ነው ያለው ኮሚሽኑ የመሳተፉ ጉዳይ የዲያስፖራዎቹ መብት ነው ሲል አሳስቧል፡፡

አዲስ አለም አበበ

ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *