የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የብሔር እና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ስያሜዎችን የሚጠቀሙ ክለቦች ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ባወጣው መመሪያ መሠረት ስሑል ሽረ ቀዳሚው ማስተካከያ ያደረገው ክለብ ሆነዋል።
በዚህም መሠረት ከዚህ ቀደም “ስሑል ሽረ እግርኳስ ክለብ” በሚል ይጠቀምበት የነበረውን መጠርያ ወደ “ሽረ ምድረገነት እግር ኳስ ክለብ” መለወጡን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል ።
ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም
