ሊቨርፑል ስዊድናዊን የፊት መስመር አጥቂ አሌክሳንደር አይሳክ ለማስፈረም ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ሙሉ ለመሉ ተሰማማ።
ኒውካስል ዩናይትድ ተጫዋቹን በ 130 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ለሊቨርፑል ለመሸጥ ከስምምነት መድረሳቸው ተዘግቧል።
አይሳክ በዛሬው ዕለት የህክምና ምርመራውን በማድረግ የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት ለሊቨርፑል የሚፈርም ይሆናል።
አሌክሳንደር አይሳክ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ በከፍተኛ ክፍያ የተዘዋወረ ቀዳሚው ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ይፅፋል።
ጋዲሳ መገርሳ
ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም
