ወላይታ ድቻ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ዋንጫን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረከቡን አስታውቋል።
ክለቡ ዛሬ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የወላይታ ድቻ የበላይ ጠባቂ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች ፣ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች በተገኙበት ዋንጫውን ተረክቧል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፅህፈት ቤት ዋንጫውን ለክለቡ አስረክበዋል።
ዋንጫው የፊታችን አርብ ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም ወደ ወላይታ ዞን እንደሚያቀና የክለቡ ደጋፊዎች ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ በዕለቱ በአደባባይ የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉም ተገልጿል።
ጋዲሳ መገርሳ
ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም
