ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 57 ሚሊዮን ብር የሚደርሱ ሽልማቶችን ያጣመረዉን የበሽ ሽልማት በይፋ አስጀመረ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለሶስት ወራት የሚዘልቅና 57 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ለሽልማት ያቀረበበትን በሽ የተባለውን የሽልማት መርኅ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አስጀምሯል።

ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የተጀመረው የበሽ ሎተሪ ሽልማት የመጀመሪያዎቹ የሁለት ሳምንታት የ1 ሚሊየን ብር አሸናፊዎች በሥነ ስርዓቱ ላይ የተሸለሙ ሲሆን በየሳምንቱ ሁለት ሰዎችን ሚሊየነር እያደረገ እስከ ሕዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም የሚዘልቅ መሆኑም ተገልጿል።

በዚህ የሽልማት መርኅ ግብር ደንበኞች ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ እና የሳምንቱ ትልቁ አሸናፊ የሚሆኑበት እንዲሁም ከእያንዳንዱ ደንበኛ የአጠቃቀም ልምድ ጋር የተሰናሰሉ አዳዲስ የበሽ ጥቅሎች መቅረባቸውንም ሰምተናል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ዋና ኃላፊ ዶ/ር  አንዱዓለም አድማሴ በሽ ጥቅል እንደተለመደው ለሁሉም ደንበኞች የሚቀርቡ ተመሳሳይ የጥቅል አማራጮችን የሚያቀርብ ሳይሆን የደንበኞችን ግላዊ የአጠቃቀም ፍላጎት በመረዳት ለእያንዳንዱ ደንበኛ የአጠቃቀም ልምድ የሚመቹ  መሆኑን ገልጸዋል።

በበሽ ሽልማት ዕለታዊ ለ224,000 አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው 100 ብር፣ ሳምንታዊ ለ25 አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው 100,000 ብር፣ ሜጋ ሳምንታዊ ለ32 አሸናፊዎች ለእያንዳንቸው 1,000,000 ብር የሚሸለሙ ሆኖ በጠቅላላው 56.9 ሚሊየን ብር ለሽልማት ቀርቧል።

ለዚህ ሽልማት ብቁ የሚሆኑት ተሳታዎች የሳፋሪኮም ደንበኞች ሆነው በስማቸው የተመዘገበ የኤም ፔሳ አካውንትና ሲምካርድ ሊኖራቸው ይገባል ሲልም ሳፋሪኮም አስታዉቀዋል።

ለአለም አሰፋ

ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *