የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለፀው፤ ጦርነቱ በፈጠረው የረሀብ ቀውስ ሳቢያ 1መቶ45 ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 4መቶ22 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡
በተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ በጦርነት ከበባው እና ተስማሚ አከባቢ ባለመኖሩ ምክንያትም በናስር ሜዲካል ኮምፕሌክስ ህጻናት መሞታቸውን አልጀዚራ በዘገባው ጠቅሷል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው የአይ ፒ ሲ ሪፖርት ባለፈው ወር በሰሜናዊ ጋዛ ረሀብ መከሰቱን ካወጀበት ግዜ አንስቶ፤ 30 ህፃናትን ጨምሮ 1መቶ44 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል ሲል አልጀዚራ በዘገባዉ አስነብቧል፡፡
ጄሩሳሌም ፖስት ይዞት በወጣዉ ዘገባ ደግሞ፤ ሃማስ በጋዛ ከተማ ውስጥ በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በመጠቀም እስራኤል ጥቃቷን እንድታቆም ዓለም አቀፍ ጫና እንዲጨምር እያደረገ ነዉ ስትል እስራኤል መክሰሷን ያሳያል፡፡
ሃማስ የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በጋዛ ከተማ የሚያደርሰውን የመሬት ላይ ጥቃት ለማደናቀፍ አንዳንድ ታጋቾችን በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ከመሬት በላይ ወደሚገኙ ቦታዎች ማዘዋወር መጀመሩን የካን ኒውስ ዘገባ አስታውቋል።
የፍልስጤም ምንጮች እንደገለጹት፤ አንዳንድ ታጋቾች በቤቶች ውስጥ ሲያዙ ሌሎች ደግሞ በድንኳኖች ውስጥ ይገኛሉ።
ይህ ስልት በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በመጠቀም እስራኤል ጥቃቷን እንድታቆም ዓለም አቀፍ ጫና እንዲጨምር ለማድረግ ያለመ ነው መባሉ ተዘግቧል።
ሀና ሰይፉ
መስከረም 5/2018 ዓ.ም
