ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስራኤል ራሷን ችላ እንድትቆም የራሷን የጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪዎች ማጠናከር አለባት ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለጀሩሳሌም ፖስት እንደተናገሩት፤ በበርካታ ሀገራት ታግዞ በእስራኤል ላይ እገዳ ለመጣል በሚደረገው ጥረት ኳታር ግንባር ቀደም ሆናለች።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤በአሁኑ ወቅት ኳታርን ጨምሮ በተለያዩ አካላት እና ሀገራት በእስራኤል ላይ እገዳ ለመጣል ሙከራ እየተደረገ ነው፤
ይህ በመጀመሪያ ደረጃ በኳታር እና እንደ ቻይና ባሉ ሌሎች ሀገራት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የሚዲያ እገዳን ያካትታል ብለዋል።
በቀጣይ አመታት በዚህ እገዳ ውስጥ ሰብረን ለመግባት የራሳችንን የጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪዎች ማጠናከር፣ የጦር መሳሪያ ምርትን እና የኢንዱስትሪ አቅማችንን ማሳደግ አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
አሜሪካ ከእኛ ጋር ነች፣ ሌሎች በርካታ ሀገራትም አሉ፤ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በምዕራብ አውሮፓ ልዩ ፈተና ገጥሞናል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንን እገዳ ለማንሳት በንቃት እየሰራን ነው እንደ ወታደራዊ እገዳው ሁሉ ይህንን የዲፕሎማሲያዊ እገዳም ማለፍ እንችላለን ሲሉ መናገራቸዉን የዘገበዉ ጀሩሳሌም ፖስት ነዉ፡፡
እስከዳር ግርማ
መስከረም 6/2018 ዓ.ም
