የኔቶ ወታደራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አድም ጁሴፔ ካቮ በላትቪያ የተካሄደው የውትድርና ኮሚቴ ጉባኤ ላይ እንዳሉት በበርካታ ሀገራት ውስጥ በቅርቡ የተፈጸመውን የሰው አልባ አውሮፕላኖች ወረራ ተከትሎ ከዚህ በኋላ ለሚመጣ ማንኛውም ስጋት ቆራጥ እና ተመጣጣኝ ምላሽ እንሰጣለን ብለዋል፡፡
የኔቶ ወታደራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢው ከላትቪያ መከላከያ ኃላፊ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ በኔቶ አየር፣ መሬት እና የባህር ክፍል ላይ የሚደርስን ማንኛውም ጥቃት በቆራጥነት እና በተመጣጣኝ ምላሽ ለማስተናገድ እኛ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
የጁሴፔ ካቮ ንግግር በቅርቡ በሩሲያ የአየር ክልላችን ጥሰዋል በማለት ስጋት ላይ የወደቁትን ፖላንድ እና ኢስቶኒያን ለማጠንከር ያለመ ነው ተብሉዋል፡፡
ካቮ እንዳሉት ግጭት አንፈልግም ነገር ግን እራሳችንን ለመከላከል አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም እርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ አንልም ሲሉም አክለዋል።
ሩሲያም በበኩሉዋ የአውሮፓ ህብረትና ኔቶ ዛቻዎችን እያሰሙብኝ ነው ስትል የከሰሰች ሲሆን ማንኛውንም ጥቃት በቆራጥነት ለመመለስ ዝግጁ ስለመሆኑዋ የዘገበው አናዱሉ ነው፡፡
መስከረም 20/2018 ዓ.ም
