በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ማርያም የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ እስካሁን በዉል ያልታወቁ ሰዎች ህይወታቸዉ ማለፉን የወረዳዉ ኮሚኒኬሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል ፡፡
ቤተክርስቲያኗ አመታዊውን የቅድስ ድንግል ማርያም የንግስ በዓል አስመልክቶ ከምታካሂደው የንግስ ክብረ በአል ጎን ለጎን እየተሰራ ያለው የቤተክርስቲያኗ ግንባታ እየተጎበኘ ባለበት ሰዓት ለፊኒሺንግ የተረበረበው እንጨት የመደርመስ አደጋ አጋጥሞታል፡፡
በዚህም በሰዎች ላይ የሞት እና የአደጋ ጉዳት መድረሱን የወረዳዉ ኮምኒኬሺን ቢሮ ሃላፊ አቶ ኑርላህ ከድር አስታዉቀዋል ፡፡
በጉዳቱ እስካሁን ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ በርከት ያሉ ሰዎች ህይወታቸዉ እንዳለፈ የገለፁ ሲሆን ርብራቡ የተጫናቸዉን ተጎጂዎች የማዉጣቱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
መስከረም 21/2018 ዓ.ም
