በሩሲያ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶች በአንድ ምሽት አምስት ሰዎች ሲሞቱ፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ያለ ኤሌክትሪክ ቀርተዋል ሲሉ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል።
በተለይም የምዕራቡን የሊቪቭ ክልል ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶች እንደደረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ የ15 ዓመትን ልጅ ጨምሮ የአንድ ቤተሰብ አራት አባላት ተገድለዋል ተብሏል።
የዩክሬን ጎረቤት ፖላንድ የአየር ክልሏን ደህንነት ለማረጋገጥ ተዋጊ ጄቶች አሰማርታ እንደነበር የፖላንድ ጦር ሲገልጽ፤ የኔቶ አውሮፕላኖችም ተሰማርተው እንደነበር ተገልጿል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዩክሬን ወታደራዊ እና የመሰረተ ልማት ዒላማዎች ላይ ግዙፍ ጥቃት በተሳካ ሁኔታ መፈጸሙን ተናግሯል።
ዘለንስኪ እንዳሉት፤ ሩሲያ ከ50 በላይ ሚሳኤሎች እና ወደ 5መቶ የሚጠጉ ድሮኖችን ተኩሳለች።
የዩክሬን አየር ኃይል አጠቃላይ አሃዙን 5መቶ49 ነዉ ብሎታል።
ጥቃቱ የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶች እና የኤሌክትሪክ አቅርቦቶች እንዲቋረጡ አድርጓል።
ይህንን የአየር ላይ ጥቃት ለማስቆም እና ምላሽ ለመስጠት፤ በአየር መከላከያ ላይ የበለጠ ጥበቃ እና ሁሉንም የመከላከያ ስምምነቶች በፍጥነት መተግበር አለብን ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ወደ እውነተኛ የዲፕሎማሲ መንገድ የሚወስደን ነዉ ማለታቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
መስከረም 26/2018 ዓ.ም
