ሐማስ በሕይወት ያሉ እስራኤላውያን ታጋቾችን በሙሉ ለቀቀ

የእስራኤል መከላከያ በሕይወት ያሉ ታጋቾች በሙሉ መለቀቃቸውን አስታዉቋል።

የእስራኤል ጦር ዛሬ ማለዳ የመጀመርያዎቹን ሰባት ታጋቾች ተረክቦ ቤተሰቦቻቸውን ወደሚያገኙበት ስፍራ እየወሰደ መሆኑን ገልጾ ነበር።

ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተጨማሪ 13 ታጋቾችን ከቀይ መስከል ተረክቦ ወደ እስራኤል እየወሰደ መሆኑን ገልጿል።

ጦሩ ባወጣው መግለጫ ላይ “የእስራኤል ጦር እና ደህንነት ኤጀንሲዎች ተመላሾቹን ወደ እስራኤል አጅበው እያመጧቸው ነው” ብሏል።

ወደ እስራኤል ከተመለሱ በኋላ “የመጀመርያ የሕክምና ምርምራ ይደረግላቸዋል” ያለው መግለጫው፤ በኋላ ላይ ለቀይ መስቀል ተላልፈው የሚሰጡ ተጨማሪ ታጋቾችን ለመረከብ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ሐማስ በበኩሉ በሕይወት ያሉ ሁሉንም ታጋቾች ማስረከቡን የገለፀ ሲሆን፤ የ28 ታጋቾች አስከሬንን በዛሬው ዕለት እንደሚያስረክብ አስታውቋል።

የእስራኤላውያኑ ታጋቾች ቤተሰቦች ደስታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለጽ ላይ ናቸው።

የታጋቾች እና የጠፉ ቤተሰቦች የተሰባሰቡበት ‘ሆስቴስ ኤንድ ሚሲንግ ፋሚሊስ ፎረም’ በማኅበራዊ ሚዲያ ገፁ ላይ “ወደ አገራችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ” ሲል ለጥፏል።

ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *