ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የባህር አጠቃቀም መሰረት የሚጥል ኮንፈረንስ ልታዘጋጅ ነው

”ዘ አፍሪካ ማሪታይም ኮንፈረንስ 2025” የመላው አፍሪካ መሪዎች እና በአለም አቀፍ የባህር ላይ ጭነት ማጓጓዣ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ መሪዎችን የሚያሳትፍ ኮንፈረንስ “አፍሪካ እና ቀጣይ የአለም አቀፍ የመርከበኞች ግንባር በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

መድረኩም አፍሪካ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪና ሁሉን ያከተተ የባሕር ላይ የሰው ኃይል ለመገንባት በጋራ በምታደርገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍን መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነም ተመልክቷል።

ጉባኤው ሚኒስትሮችን፣ የቁጥጥር አካላትን፣ የመርከብ አስተዳደር ኃላፊዎችን፣ የባሕር ላይ አካዳሚዎችንና የልማት አጋሮችን የሚያሰባስብ ሲሆን፣ የኮንፈረንሱ ራዕይ ፖሊሲ እና አጋርነትን ለማቀራረብ አፍሪካ ለዓለም አቀፉ የባሕር ላይ ኢኮኖሚ ቋሚ አበርክቶ እንዳላት ለማሳየት ያለመ ነው ተብሏል፡

በዚህ ኮንፈረንስም መንግሥታት የሥልጠና፣ የሥራ ዕድልና ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚያገናኝ ዘላቂ የባሕር ላይ ሥነ-ምህዳር ለመንንባት ያለውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ምን መምሰል እንዳለበትም ያቀርባሉ።

ኮንፈረንሱ ከጥቅምት 4 እስከ 6 2018 ዓ.ም ለ3 ቀናት በአዲስ አበባም እንደሚካሄድ ሲገለጽ፤

ዋይ ሲ ኤፍ ማኒንግ ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ጋር በአጋርነት ያዘጋጁት ኮንፈረንስ እንደሆነም ሰምተናል።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *