የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ በ80 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የቤተሰብ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ኦዲንጋ ረቡዕ እለት ሕንድ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ነው ማረፋቸው የተሰማው።

ምንም እንኳ ከቅርብ ጊዜያት በኋላ በጠና መታመማቸውን የሚገልጹ ሪፖርቶችን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ውድቅ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በኬንያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ሰው የነበሩት ኦዲንጋ፤ አምስት ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ቢወዳደሩም ሳይሳካለቸው ቀርቷል።

በተደጋጋሚም ውጤቴ ተሰርቆብኛል በማለት ክስ ከማቅረብ ጀምሮ በሀገሪቱ ከፍተኛ የንብረት እና የሰው ህይወት የቀጠፉ የአደባባይ ሰልፎችን አስተባብረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *