የአፍሪቃ ሕብረት ማዳጋስካር ዉስጥ ተደረገ ያለዉን መፈንቅለ መንግሥት አወገዘ።
ሕብረቱ ትናንት ባወጣዉ መግለጫ የማዳጋስካር ጦር ኃይል የሐገሪቱን የመንግሥትነት ሥልጣን መያዙን ተቃዉሟል።
ሕብረቱ ከዚሕ ቀደም ወታደራዊ መፈንቅለ-መንግሥት በሚደረግባቸዉ አባል ሐገራት ላይ እንደሚያደርገዉ ሁሉ ማዳጋሥካርን ለጊዜዉ ከአባልነት አግዷልም።
በሐገሪቱ ዉስጥ ባስቸኳይ ምርጫ እንዲደረግና የሲቪል አስተዳደር እንዲመለስ ሕብረቱ አሳስቧልም።
አዲሱ የማዳጋስካር ወታደራዊ መሪ ኮሎኔል ማይክል ራንድርያኒሪና ነገ አርብ ቃለ መሐላ ፈፅመዉ የመሪነቱን ሥልጣን በይፋ እንደሚይዙ አረጋግጠዋል።
የማዳጋስካር ጦር-ኃይል የአስተዳደርና የቴክኒክ አገልግሎት ጓድ (CAPSAT) አዛዥ ኮሎኔል ራንድርያኒሪና የፕሬዝደንት አንድሬይ ራጆሊናን አስተዳደር ይቃወሙ ነበር።
የ51 ዓመቱ ኮሎኔልና የሚያዙት ጦር ባልደረቦች የማዳጋስካር ወጣቶች የራጆሊናን አስተዳደር በመቃወም በተከታታይ የሚያደርጉትን ሠልፍ በግልፅ የተቀየጡት ባለፈዉ ቅዳሜ ነበር።
ወጣቶቹ የፕሬዝደንት ራጆሊናን አስደደር የተቃወሙት የኑሮ ዉድነት፣ሥራ አጥነት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ሥላስመረራቸዉ ነዉ።
የፀጥታ ኃይላት ተቃዉሞዉን ለማዳፈን በወሰዱት የኃይል እርምጃ ከ20 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።አመፁ በማየሉ ከሐገር የሸሹት ወይም የተሰወሩት ፕሬዝደንት ራጆሊና ጦር ኃይሉ ሥልጣን መያዙት ተቃዉመዋል ሲል DW ዘግቧል።
ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም
