ትራምፕ በቡዳፔስት ከፑቲን ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ስብሰባ እንደሰረዙ ተናግረዋል ።
“ወደ ፊት ግን (ስብሰባውን) እናደርገዋለን” ሲሉም አክለዋል።
ቀደም ብለው በወጡ ዘገባዎች ትራምፕ አስተዳደራቸው ዩክሬን በምዕራቡ ዓለም የሚቀርቡ የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን በመጠቀም ሩሲያ ውስጥ የሚገኙ ኢላማዎችን እንድትመታ ፈቅዷል የሚሉ ዘገባዎችን ውድቅ ማድረጋቸውን አትተዋል።
ትራምፕ የዎል ስትሪት ዘገባ ሀሰተኛ ዜና ነው ሲሉ በትሩዝ ሶሻል ገፃቸው አመልክተዋል።
በሌላ ዜና አሜሪካ በሩሲያ ግዙፉ የነዳጅ ኩባንያዎች ሮዝኔፍት እና ሉኮይል ላይ ማዕቀብ መጣሏንም ስፑትኒክ ዘግቧል ።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት ሁለቱ ቡድኖች ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግጭቱን ለማስቆም ጥረት እያደረጉ ባለበት ወቅት፤ “የክሬምሊንን የጦር ማሽን በገንዘብ እየደገፉ” ይገኛሉ ብለዋል።
ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም
