ምክር ቤቱ ባደረገው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ግምገማ፤ በ2017 የበጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ አፈፃፀም በጥንካሬው በመቀጠል 9.2 በመቶ ዓመታዊ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) እድገት አሳይቷል ብሏል።
እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ ብሎም የማዳበሪያ ማምረቻ እና የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ሥራ ጅማሮዎች የኢኮኖሚ እድገቱን የበለጠ እንደሚያነቃቁ ተገልጿል፡፡
የየዘርፉ የእድገት ትንበያም ጠንካራ ውጤት እንደሚገኝ ያመለከተ ሲሆን፦በግብርና በ7.8 በመቶ፣ በኢንዱስትሪ 13.2 በመቶ እና በአገልግሎት ዘርፉ 9.3 በመቶ እድገት ይጠበቃል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት በሦስት ወራት ብቻ 6.5 ትሪሊየን ብር ተንቀሳቅሶበታል፡፡
የሀገሪቱ የውጭ ንግድ 2.5 ቢሊዮን ዶላር በመድረስ ከእቅዱና እና በባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ከነበረው አፈፃፀም የበለጠ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም
