የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ፓርቲ የምስረታ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ

የፓርቲው አደራጅ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በጉባኤው ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፥ የትግራይን ህዝብ ህልውና ለማስጠበቅ መስራት አለብን ብለዋል።

ፓርቲው እስካሁን ከ5 ሺህ 6መቶ በላይ አባላት መመዝገቡን ጠቅሰው፥ አባላቱ በምስረታ ጉባኤው ላይ መሳተፍ ቢፈልጉም በፀጥታ ችግር መምጣት እንዳልቻሉ አንስተዋል።

ፓርቲው የትግራይ ህዝብ በህወሓት እየደረሰበት ያለውን ጫና በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መመስረቱን የገለጹ ሲሆን፤ ህወሓት ከሌሎች የውጪ አካላት ጋር በመቀናጀት በክልሉ ብሎም በሀገር ሰላም ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።

እየተካሄደ ባለው ጉባኤ 2መቶ56 አባላት ድምፅ በመስጠት እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡

ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ በበኩላቸው ላለፉት 50 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ አካል የነበረው ህወሓት የትግራይን ህዝብ የፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ስምረት ፓርቲ በኃይል ሳይሆን በሀሳብ ላይ የተመሰረተ ትግል ለማድረግ መመስረቱ የትግራይ ህዝብ ሰላም ፈላጊነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በምስረታ ጉባኤው ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለሰ ዓለሙ፥ ለኢትዮጵያ መፃኢ የብልፅግና ጉዞ ስምረት ፓርቲ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *