ኢትዮጵያ ሰማይ ተከፍቶላታል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

ለዚህም ምክንያቱ አሁን በሀገሪቱ ውስጥ የእሳቤ ለውጥ ስለመጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብየረ ፤ ኢትዮጵያ እየተመራችበት ባለው መንገድ በ2032 በአፍሪካ ሁለተኛ ትልቋ ኢኮኖሚ፤ በ2036 ደግሞ ቀዳሚዋ ኢኮኖሚ እንደምትሆን አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሜጋ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ፣ ማዳበሪያ፣ አውሮፕላን ማረፊያና ቤቶች ልማት ላይ የምንሰራው ስራ ጨዋታ ቀያሪ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የማዳበሪያ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ብቻ የግብርና ምርታማነትን ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸው፣ ይህም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ትልቅ እጥፋት ነው። ሌሎችም ሲጠናቀቁ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ይመጣል ብለዋል

የሰራነውን ጥንካሬ እናስቀጥላለን ድካሞቻችንን ደግሞ እያረምን ፣ እያረቅን ፣ እያሻሻልን እንሄዳለን። የናተን ግብዓትም እንጠቀማለን። የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በዚህ መንገድ ጥቆማ ስትሰጡ ይጠቅመናል ያላየነውን ነገር ለማየት የሚያግዝ ስለሆነ በጥሩ መንፈስ የምንወስደውና የምንሰራበት ነው። “

ለዓለም አሰፋ

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *