አብዛኛዉ ህጻናት እና ሴቶች የሆኑ ወደ ከ1መቶ የሚበልጡ ፍልስጤማዊያን ከተገደሉ በኋላ በተኩስ አቁሙ ላይ ተስፋ እያጣን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነቱ አሁንም ጠንካራ ነው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡
ሂደቱን ስታሸማግል የቆየችዉ ኳታር በጉዳዩ መበሳጨቷን ብትገልጽም፤ አሸማጋዮቹ ቀጣዩን የእርቅ ሂደት በጉጉት እየጠበቁ ነው ተብሏል።
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ አንድ ወታደሯ በሀማስ ተገሎብኛል በማለት የበቀል እርምጃ ወስጃለሁ ስትል ያስታወቀች ቢሆንም፤ሃማስ በበኩሉ ለጥቃቱ ተጠያቂ አይደለሁም ብሏል ሲል የዘገበዉ አልጀዚራ ነዉ።
ሀና ሰይፉ
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
