ከ11 ሺህ የተሻገሩ እግረኞች በአዲስ አበባ ከመንገድ አጠቃቀም ስርአት ጋር በተያያዘ መቀጣታቸው ተገለፀ

በአዲስ አበባ የመንገድ ትራንስፖርት ለመቆጣጠር የወጣዉን ደንብ 557/2016 11 ሺህ 508 እግረኞች ተላልፈዉ መገኘታቸዉ ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ትራፌክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ገነት ዲባባ እንደገለፁት ይህ ቁጥር በሶስት ወራት በእግረኞች ላይ በተካሄደው ቁጥጥር የተገኘ መሆኑን አስረድተዋል።

እነዚህ እግረኞች ትክክለኛ የመንገድ አጠቃቀም ያልተከተሉ ሆነዉ በመገኘታቸዉ 6 ሺህ አንድ መቶ ስምንት የሚሆኑት በገንዘብ እንዲቀጡ ተደርጓል።

እንዲሁም 5 ሺህ 499 እግረኞች ደግሞ ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ተቀጥተዋል ተብሏል።

የጆሮ ማዳመጫ አድርገዉ መንገድ በማቋረጥ እንዲሁም ለእግረኞች ተብለዉ የተተከሉ አጥሮችን የዘለሉ እግረኞች በቅጣቱ እንደምክንያት መቀመጡን ተገልፆል።

የእግረኛ መንገድ በሌለበት ቀኝ ጠርዝ ይዘዉ የተጓዙ ÷ በትክክለኛ የእግረኛ መሻገሪያ መንገድ ያላቋረጡ እንዲሁም ደግሞ በተሽከርካሪ መንገድ ያለ በቂ ምክንያት በቆሙ እግረኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ በተጨማሪም ከ 100 እስከ 150 ብር እንዲቀጡ መደረጉን ሰምተናል።

ቁምነገር አየለ

ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *