በሚቀጥሉት 30 እና 40 ዓመታት ከሀገሪቱ ህዝብ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው በከተማ ይኖራል ተብሎ ይገመታል ሲሉ ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ከ73 ከተሞች በላይ በኮሪደር ልማት እየተሳተፉ እንደሆነና ይህም ከተሞች የራሳቸውን የገቢ አቅም ለማሳደግና ለዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩበትን ምቹ ሁኔታ እየፈጠረላቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
መንግሥት ከተሞችን የድህነት፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና የሥራ አጥነት ማሳያ ሳይሆን፤ የብልጽግና ማሳያ እናደርጋቸዋለን ብሎ አቅዶ እየሠራ ይገኛል ሲሉ 10ኛውን የከተሞች ፎረም አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ለሚዲያዎች ተናግረዋል፡፡
ህዳር 03/2018 ዓ.ም
