የቀድሞዋ የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው።

በሽሽት በህንድ የሚገኙት ሼክ ሀሲና “በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀመ ወንጀል” ተከሰው በሌሉበት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

የባንግላዴሽ ከፍተኛ ፍርድቤት ጠቅላይ ሚኒስትሯ በስልጣን በነበሩበት ወቅት በመንግሥታቸው ላይ ተቃውሞ ባስነሱ ዜጎች ላይ ግድያ እንዲፈፀም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ተማሪዎች ባስነሱት አመፅ ተገደው ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ወደህንድ ሸሽተዋል።

ከሼክ ሀሲና በተጨማሪ የቀድሞው የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አሳዱዝማን ከማል እና የሀገሪቱ የፖሊስ አዛዥ ቾውዱሪ አብዱላህ ላይም ተመሳሳይ የሞት ፍርድ ማስተላለፉን ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡

ልዑል ወልዴ

ህዳር 08/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *