የትራፊክ አደጋ በዓመት 1 ነጥብ 2 ሚሊዬን ሰዎችን ይገድላል ተባለ

የትራፊክ አደጋ በአለም ላይ በዓመት 1 ነጥብ 2 ሚሊዬን ሰዎችን እንደሚገድል ጥናት አመላከተ

በጥናቱ መሰረት በአዲስ አበባ በ2024/25 ፤ 448 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።

ይህም ከመቶሺ ሰዎች ውስጥ 7 ነጥብ 9 በመቶ ሞት ይመዘገባል ነው ያሉት።

አደጋው በዋናነት እግረኞችን፣ብስክሌተኞችን እና ሞተረኞችን ሰለባ እንደሚያደርግ በቢገርስ ተቋም የመንገድ ደህንነት የመረጃና የክትትል አስተባባሪ ሜሮን ጌታቸው ተናግረዋል።

እንደ ጥናቱ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት ዜጎች በአደጋው እጅግ ተጎጂው ናቸው የተባለ ሲሆን ከፍተኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት በ2 እጥፍ የሚበልጥ አስከፊ አደጋንም ያስተናግዳሉ ሲሉ ባለሙያዋ አስረድተዋል፡፡

በተደጋጋሚና በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ ይከሰትባቸዋል ብለው ከዘረዘሯቸው አከባቢዎች መካከል መገናኛ፣ቦሌ ሚካኤል ወሰን መንገድ ሃይሌ ግራንድ አካባቢ ፣ቃሊቲና ጀሞ ይገኙበታል ብለዋል።

ባለሙያዋ ይህን የገለፁት በኢትዮጵያ የትራፊክ ተጎጂች ወር ለ18ኛ ጊዜ እየተከበረ ባለበት ወቅት ነው።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን”እናስታውስ ፣እንደግፍ ፣ለለውጥ እንስራ “በሚል መሪ ቃል የትራፊክ ተጎጂዎችን ወር እየተከበረም ይገኛል።

ባለስልጣኑ የህዳር ወር ሙሉ የትራፊክ ተጎጅዎች የሚታሰቡት ወር ሆኖ እንደሚውልም አስታውቋል።

የትራፊክ ተጎጅዎች ወር በኢትዮጵያ ለ18ኛ ጊዜ በዓለም ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ እየተከበረ መሆኑንም ሰምተናል ።

ልኡል ወልዴ

ህዳር 11/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *