ለህፃናት የሚሰጠው የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት መርሀ ግብር ይፋ ሆነ

ይህ ክትባት ህፃናት እንደተወለዱ በ24 ሰዓታት ውስጥ የሚሰጥ ነው፡፡

ክትባቱ በተለይ ከእናቶች ወደ ልጅ የመተላለፍ መጠኑ ከፍተኛ የሆነውን የጉበት በሽታ ለመከላከል አስፈላጊነቱ የጎላ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ የተጀመረውን ይህንን መከላከያ ክትባት ተዳራሽ በማድረግ እንደሚሰራ እና ህፃናቱ ይህንን ክትባት እንዲወስዱ በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶችን ማበረታታት እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር በዛሬው እለት ይህንን መርሀ ግብር በአበበች ጎበና የእናቶችና ህጻናት ሆስፒታል አስጀምሯል፡፡

ህጻናት እንደተወለዱ የሚሰጠው ይህ ሀገር አቀፍ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት ጤናማ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ወሳኝ ሚና እንዳለው ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም እንደ ሀገር የበሽታው ተጋላጭነትን ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተው በተለይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ክትባቱን ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

አዲስአለም አበበ

ህዳር 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *