በኪየቭና ሮስቶቭ በተፈጸሙ ጥቃቶች 5 ሰዎች ተገደሉ::

በሩሲያና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ በሁለቱም አቅጣጫ በተፈጸሙ ጥቃቶች የሰዎች ሞትና ጉዳት እንደደረሰ ተገልፅል።

አለም አቀፍ የዜና አውታሮች እንደዘገቡት፣ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ እና በሩሲያ ከተማ ሮስቶቭ ላይ በተፈጸሙት ጥቃቶች ቢያንስ አምስት 5 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

በኪየቭ ላይ የተፈጸመው ጥቃት በሩሲያ ኃይሎች የተሰነዘረ ሲሆን፣ በከተማይቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሰዎች መኖሪያ ቤቶች እና መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።

በተመሳሳይ ጊዜ፣ ዩክሬን በሩሲያ ከተማ ሮስቶቭ ላይ የደረሰውን ጥቃት ፈጽማለች ተብሎ ተጠርጥሯል የሩሲያ ባለሥልጣናት እንደገለጹት፣ በጥቃቱ ንፁሐን ዜጎች የተጎዱ ሲሆን፣ አንዳንድ የመኖሪያ እና የንግድ ሕንፃዎች ላይ ውድመት ደርሷል።

ሁለቱም ወገኖች በተቃራኒው አካባቢዎች ላይ ወታደራዊ እና የኃይል አውታሮችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን ማካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ሥፍራው ላይ የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን አመልክተዋል።

ሩሲያም ሆነች ዩክሬን በአንዳቸው ከተሞች ላይ የንጹሐን ዜጎችን ሞት የሚያስከትሉ ጥቃቶችን በመፈጸም እርስ በእርስ ይወነጃጀላሉ መበሉን አልጀዚራ ዘግቦል።

ሱፊያን አህመ

ህዳር 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *