ኢቲ-ስዊች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የዲጂታል የገንዘብ ዝውውርን የሚያጠናክር የ5 ዓመት ስትራቴጂ ስምምነት ተፈራረመ

የክፍያ ጥያቄዎችን በባንኮች፣ በካርድ ኔትወርኮች እና በክፍያ አገልግሎት አቅራቢዎች መካከል የሚያገናኝ ስርአት ላይ የሚሰራው ኢትስዊች፤ ተግባሩን አለም አቀፋዊ ለማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ከጀነሲስ አናሊቲክስ ጋር ተፈራርሟል።

በስምምነት መድረኩ ላይ የተገኙት የኢትስዊች ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ይለበስ አዲስ ፤ ኢትስዊች ስትራቴጂውን ሊያዘጋጁ የሚችሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን አወዳድሮ ጀነሲስ አናሊቲክስን መመረጡን አስረድተዋል።

ስትራቴጂው ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የዲጂታል የገንዘብ ዝውውር ሥርዓቱን የሚያጠናክሩ መፍትሄዎች እንደሚኖሩትም ገልፀዋል።

በተጨማሪም ኢቲስዊች ተናባቢነትን መፍጠር፣ የሀገር ውስጥ የክፍያ ስርአትን ማዘመንና የፋይናንስ ተቋማት በጋራ የሚጠቀሙበትን መሰረተ ልማት መፍጠርን ግብ ያደረገው አላማ ነው ተብሏል ።

በተለይም መሰል ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሰሯቸውን ክንውኖች በመመልከት እንደ ብሔራዊ ስዊች ምን ማድረግ እንደሚጠበቅ ትኩረት ተደርጎበታል።

ኢትስዊች የኢትዮጵያ ባንኮች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ስርአት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።

ልኡል ወልዴ

ህዳር 17/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *