ብድሩ በ31 ዓመት ጊዜ ዉስጥ የሚከፈል መሆኑም ተገልጿል፡፡
በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለዘላቂና ንጹህ ኢነርጂ ተደራሽነት ለውጥን ለማፋጠን ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረገውን የ2መቶ94 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው በአምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ የብድር ስምምነቶችን ማጽደቁ ተገልጿል፡፡
በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለዘላቂና ንጹህ ኢነርጂ ተደራሽነት ለውጥን ለማፋጠን ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረገውን የ2መቶ94 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ፤አዋጅ ቁጥር 1398/2018 በማድረግ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚንስትር ተስፋዬ በልጅጌ፤ 2መቶ94 ሚሊየን ዶላሩ ስድስት ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ31 ዓመታት ውስጥ የሚከፈል መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ትራንስፎርሜሽን እና ቀጣናዊ ውህደት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ተጨማሪ የብድር ስምምነትን ረቂቅ አዋጅ፤አዋጅ ቁጥር 1399/ 2018 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የመንግስት ተጠሪ ሚንስትሩ፤ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር የተገኘውን የ20 ሚሊየን ዶላር ብድር ከወለድ ነጻ መሆኑን ገልጸው ፤ የስድስት ዓመታት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ የሚከፈል መሆኑን ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።
ህዳር 25/2018 ዓ.ም
