በላፍቶ ክፍለከተማ የተጀመረውን ይህን ግንባታ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስጀምረዋል።
ከንቲባ አዳነች በግንባታ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ‹‹በዚህ ዓመት ከያዝናቸው ዋነኛ ዕቅዶች መካከል ቀዳሚው ለከተማችን ነዋሪዎች የቤት አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ነው›› ብለዋል።
በመሆኑም በዚህ ዓመት ከ1መቶ ሺህ በላይ ቤቶችን ለመገንባት አቅደን በርካታ ተግባራትን እያከናወንን ሲሆን፤ እቅዳችንን በጥራትና በፍጥነት እውን ለማድረግ ለአገራችን የመጀመሪያ የሆነውን Cold-Formed Steel (CFS) የግንባታ ቴክኖሎጂን መጠቀም አንድ አማራጭ አድርገን ዛሬ ስራ አስጀምረናል ብለዋል።
ቴክኖሎጂው በሌላው ዓለም የተለመደ ነው የተባለ ሲሆን፤ ቤቶችንም ሆነ ህንፃዎችን በፋብሪካ ውስጥ የሚገጣጠሙ ብረቶችን በመጠቀም ወለልን፣ ግድግዳና ጣሪያን ጨምሮ ሁሉንም ክፍል በፍጥነትና በጥራት ማምረት የሚያስችል አሰራር ነውም ተብሏል።
ህዳር 25/2018 ዓ.ም
