የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ“ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት)” ሕጋዊ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሰጥቷል።
ቦርዱ በዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ስምረት ሕጋዊ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም መስጠቱን አስታውቋል።
በቀድሞው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የተመሠረተው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ፓርቲ በጥቅምት ወር አቶ ጌታቸው ረዳን ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።
ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የተሰጠው ፖርቲው፤ በትግራይ ክልል አዲስ የፖለቲካ እይታ ለማቅረብ እና “ህወሓትም ሆነ ኢህአዴግ በዓለም ማሕበረሰብ ዘንድ ይቀርብባቸው የነበረ ሂስን ከመሰረቱ ለሚያርም” የተመሰረተ መሆኑን መስራቾቹ ገልጸዋል።
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
