የወላይታ ህዝብ የአዲስ ዓመት ፌስቲቫል ‹‹ጊፋታ‹‹ በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት ትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተመዘገበ፡፡

ድርጅቱ 2ዐኛው የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ጥበቃ የመንግስታት ኮሚቴ ስብሰባ ከታህሳስ 8 እስከ 13/2025 ድረስ በህንድ ኒው ዴልሂ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው ጉባኤዉ ጊፋታን በዓለም ቅርስነት መዝግቦታል፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ ጉባዔ በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችው የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ጊፋታ በዩኔስኮ በሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡

ዩኔስኮ ቅርሶችን በሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለመመዝገብ ያስቀመጣቸውን አምስት መመዘኛዎች አሟልቶ በመገኘቱ ጊፋታ በማህደሩ ለመመዝገብ ችሏል፡፡

ጊፋታን በሰው ልጆች ቅርስነት እንዲመዘግብ ካበቁት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል በዓሉ እድሜ፣ ፆታ፣ ሀይማኖትና ማህበራዊ ደረጃን ሳይለይ የሚያሳትፍ መሆኑ፣ በዓሉ ሰላምን፣ አንድነትን እና አብሮነትን የሚያበረታታ መሆኑ፣ ለዘላቂ ልማት፣ የምግብ ዋስትናን ከፍ በማድረግና አካባቢን ከመጠበቅ አንፃር ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑ እና ቅርሱ በሀገሪቱ ብሔራዊ ምዝገባ ውስጥ የተካተተ መሆኑ የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ፤ይህ በዩኔስኮ የተሰጠ ዕውቅና ለዎላይታ ሕዝብና ለኢትዮጵያ ጥልቅ ትርጉም አለው ያሉ ሲሆን፤ ይህን ቅርስ ለመጠበቅ ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *