የትራምፕ አስተዳደር አንጋፋ ዲፕሎማቶችን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ አዘዘ

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ሀገራት በአምባሳደርነትና በከፍተኛ የዲፕሎማሲ እርከን ላይ የሚገኙ 30 የሚጠጉ አንጋፋ ዲፕሎማቶችን በአስቸኳይ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

ከእነዚህ ዲፕሎማቶች መካከል ግማሽ ያህሉ (15ቱ) በአፍሪካ ሀገራት ተመድበው የሚሰሩ መሆናቸው ውሳኔው በአህጉሪቱ ላይ ያለውን ትኩረት አጉልቶታል።

የውሳኔው ዓላማ የፕሬዝዳንት ትራምፕን “አሜሪካ ትቅደም” (America First) ፖሊሲ በተግባር ለመተርጎም የታለመ ሲሆን፤ ነባር ዲፕሎማቶችን በአዲስና ከአስተዳደሩ ርዕዮተ ዓለም ጋር በሚጣጣሙ ግለሰቦች ለመተካት የታቀደ ነው።
አስተዳደሩ የሀገሪቱን የውጭ ጉዳይ ተልዕኮ በአዲስ መልክ ለመቅረጽ መወሰኑን ገልጿል።

ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ የተጠሩት ባለሙያዎች በዘርፉ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉና ሰፊ ልምድ ያላቸው መሆናቸው ይታወቃል።

ይህም በአሜሪካ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ባለው የቆየ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ ምን ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ ይችላል የሚለው ጉዳይ በዓለም አቀፍ ተንታኞች ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል እንደ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘገባ።

ልዑል ወልዴ

ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *