የኬንያው ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶ ለአንድ ቀን ጎብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር ) የኬንያዉን ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መቀበላቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሳውቀዋል፡፡

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ሲሉም ገልጸውታል።

ውይይታችንም የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የተለዋወጥን ሲሆን፤ ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ።

ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *