በኢትዮጵያ ወጥ የሆነ የመሬት ፖሊሲ አለመኖር በዜጎች የመብት ጥያቄ ላይ ተግዳሮት መፍጠሩ ተገለጸ

በኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆነው የህዝብ ክፍል ኑሮው ከመሬት ጋር የተቆራኘ ቢሆንም፤ በአገራችን እስካሁን ድረስ ራሱን የቻለ የመሬት ፖሊሲና አጠቃላይ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ አለመኖሩ በምርታማነትና በዜጎች የካሳ መብት ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህሩ ዶክተር መለሰ ዳምጤ ለጣቢያችን እንደገለጹት፤ በአገራችን የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን የሚመራ ግልጽ ፖሊሲና የተቀናጀ ዕቅድ ባለመኖሩ ዘርፉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ይገኛል።

ምንም እንኳን አንዳንድ ክልሎች የራሳቸውን መመሪያ ለማውጣት ቢሞክሩም፤ አፈጻጸሙ ግን አሁንም ድረስ ወጥ ያልሆነ አሰራር የተጋረጠበት መሆኑን አመልክተዋል።

በተለይም በልማት ምክንያት ከመሬታቸው የሚፈናቀሉ ዜጎች የሚከፈላቸው የካሳ መጠን ሌላኛው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።

እንደ ዶክተር መለሰ ማብራሪያ፤ በኢትዮጵያ መሬት የመንግስት በመሆኑ፣ ካሳ የሚከፈለው በመሬቱ ላይ ለለማው ንብረት እንጂ ለመሬቱ አይደለም።

ይህም ከቦታው መገኛ አኳያ ሊገኝ የሚችለውን የገበያ ዋጋና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላገናዘበ በመሆኑ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የካሳ ግመታው በገለልተኛ አካል ሳይሆን በመንግስት አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ብቻ መከናወኑ፤ ለግልጽነትና ለተጠያቂነት ክፍተት መፍጠሩን የሕግ ባለሙያው ጠቁመዋል።

ይህም በዜጎች ላይ የሚስተዋሉ የሕግ ጥሰቶችንና ሕገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎችን እያባባሰ ይገኛል ተብሏል።

ልዑል ወልዴ

ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *