የትምህርት ሥርዓአቱን ለማገዝ የሚያስቸል ስምምነትን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሜያለሁ ሲል ሪች ፎር ቼንጅ አስታወቀ

ሪች ፎኤ ቼንጅ ለትርፍ ያልተቋቋመ ዓለምአቀፋዊ ግብረ ሰናይ ደርጅት እንደሆነ የገለፀ ሲሆን፣ በዋናነትም በማህበረሰቡ ወስጥ የሚስተዋሉ ችግሮቸን ለመፍታት የሚንቀሳቀሱ ሥራ ፈጣሪዎችን አግዛለሁ ብሏል።

ድርጅቱ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የትምህርት ሥርዓአቱን ለማገዝ የሚያስቸል የመግባቢያ ሰነድ ታህሳስ 21፣ 2018 ከትምህርት ሚኒስቴር ተፈራርሜያለሁ ነው ያለው።

ሪች ፎር ቼንጅ የትምህርት አጋዥ መተግበርያዎችን እና መፍትሄዎችን (EdTech Solution) የፈጠሩ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን አቅማቸውን በማጎልበት፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል።

በሌላ በኩል ድርጅቱ ቆሻሻን ወደ ንግድ ሥራ የቀየሩ ሥራ ፈጣሪዎችን እየደገፈ እንደሆነ ገልጿል። የሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር መቅድም ጉልላት ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ድርጅቱ ቆሻሻን ወደ ንግድ ሥራ የቀየሩ ሥራ ፈጣሪዎችን በሚደግፍ ፕሮጀክት ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ አስተዋፅዖ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ በሁለት መልኩ የሚከናውን ነው ያሉት ዳይሬክተሯ አንደኛው አካል ቆሻሻን ወደ ንግድ ሥራ የመቀየር ሃሳብ ያላቸውን መደገፍና ሃሳባቸው ወደ ገንዘብ እንዲቀይሩ ማስቻል እንደሆነ የገለፁ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሃሳባቸውን ተግባራዊ አድርገው ቢዝነስ የመሰረቱትን ስራቸውን የማሳደግ ተግባር ነው ብለዋል።

ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ወደ ሥራ ለመግባት ስለሚቸገሩ ፕሮጀክቱ በምን መልኩ ሃሳባቸውን መሬት ማውረድ እንደሚችሉ እና ብቁ እንዲሆኑ ማገዝ ላይ እንደሚያተኩር መቅድም ተናግረዋል።

በዚህም ድርጅቱ ለጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎቹ ስልጠና መስጠት፣ የገበያ ትስስር መፍጠር፣ አብረዋቸው ለመስራት የሚፈልጉ ባለሃብቶችን ማገናኘትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የመሳሰሉ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል።

አዲስአለም አበበ

ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *