ፖርቹጋላዊው በህዳር 2024 የቀያይ ሰይጣናቱ ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ በግንቦት ወር በስፔን ቢልባኦ በተካሄደው የዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ ቡድኑን መምራታቸው ይታወሳ።
ማንቸስተር ዩናይትድ በአሁኑ ወቅት በፕሪምየር ሊጉ 6ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የክለቡ አመራሮች ለውጥ ለማድረግ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው የሚል ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። ይህ ውሳኔ ደግሞ ቡድኑ በሊጉ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ ዕድል እንደሚሰጠውም ታምኖበታል። ስለዚህ እሳቸውን ማሰናበት ተመራጭ ሆኗል።
ክለቡ ሩበን አሞሪ ለቡድኑ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋናውን እያቀረበ፣ ለወደፊት ህይወታቸውም መልካሙን ሁሉ እንደሚመኝላቸው በመግለጫው አስታውቋል።
ቀያይ ሰይጣናቱ የፊታችን ረቡዕ ወደ ተርፍሙር አምርተው ከበርንሌይ ጋር ምሽት 5:15 የሚያደርጉትን ጨዋታ የቀድሞ ኮከባቸው ዳረን ፍሌቸር ቡድኑን በጊዜያዊነት የሚመራ ይሆናል።
ምስጋናው ታደሰ
ህዳር 27/2018 ዓ.ም
