የዩኤስኤስ የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ በኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጀች ነው

የዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከን የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ከ1-2 ባሉ ቀናት ውስጥ በኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጁ እንደምትደረግ ተገልፁዋል፡፡

የአሜሪካ ጦር በክልሉ ያለውን የጥቃት ቡድን ለማጠናከር ተጨማሪ 12 የጦር አውሮፕላኖችን መላኩም ተዘግቧል።

ቀደም ብሎ ፎክስ ኒውስ የአሜሪካ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከን የአውሮፕላን ተሸካሚ የጥቃት ቡድን በህንድ ውቅያኖስ በኩል ወደ ሴንትኮም (CENTCOM) የኃላፊነት ክልል ገብቷል።

ከዚህ ቀደም ጥር 22 ቀን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ባህር ኃይል መርከቦች “ለጥንቃቄ ያህል” ወደ ኢራን እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።

ነገር ግን በወቅቱ ፣ በኢራን ላይ የሚደረገው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት አማራጭ ተሰርዟል ወይ ለሚለው ጥያቄ ግልጽ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበሩም፤ ይልቁንም ወደፊት ምን እንደሚከሰት መናገር እንደማይችሉ ብቻ ገልጸው ነበር ዘገባው የስፑትኒክስ ነው፡፡

ሀና ሰይፉ

ጥር 19/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *