ከቀበና አደባባይ አስከ ጀርመን ኤምባሲ የመንገድ ስራ እየተከናወነ በመሆኑ ለቀጣይ 15 ቀናት መስመሩ ዝግ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በአከባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ሲባል፡-
አሽከርካሪዎች:_
- ከአራት ኪሎ እና መገናኛ ወደ ጀርመን ኤምባሲ ለመሄድ በቀበና አደባባይ እና በሚኒሊክ ሆስፒታል አማራጭ መንገድ ተጠቀሙ
- ከጀርመን ኤምባሲ ለምትመጡ የሚኒሊክ ሆስፒታል መስመርን እንድትጠቀሙ በአክብሮት እንጠይቃለን ብሏል የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፡፡
ጥር 21/2018 ዓ.ም
