በወልቃይት አካባቢ ያሉ ተፈናቃዮች አሁንም አለመመለሳቸዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ

የወልቃይት ጉዳይ በሕዝብ ድምፅ ነዉ መወሰን ያለበት ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ

“እኔም አልወሰንም፣ እናንተም አትወስኑም፣ መወሰን ያለበት የወልቃይት ሕዝብ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል፡፡

በሌሎች አካባቢዎች የነበሩ ተፈናቃዮች እየተመለሱ እንደሆነና አስቸጋሪ የሆነዉ ግን በወልቃይት አካባቢ ያሉ ተፈናቃዮች ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ማለት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸዉ መመለስ ስላልፈለጉ ሳይሆን፤ ተፈናቃይን መያዣ ያደረገ ፓለቲካ ኢትዮጵያ ዉስጥ በመኖሩ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

የኔ ቢጤዎች ልጆቻቸዉን መለመኛ እንደሚያደርጉት አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎችም ተፈናቃዮችን የራስ ህልዉና ማቆያ እያደረጓቸዉ ነዉ ብለዋል።

ይህን ለማሻሻል ብዙ ሙከራ መደረጉንና ወልቃይትን በሚመለከት በአማራና በትግራይ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በመኖሩ ፌደራል መንግስት ዉሳኔዉን ለህዝብ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

“እኔም አልወሰንም፣ እናንተም አትወሱንም፣ መወሰን ያለበት የወልቃይት ሕዝብ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል፡፡

በዚሁ ምክንያት ባለፉት ዓመታት የወልቃይት ህዝብ ተገቢዉን በጀት አለማግኘቱ ተነስቷል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል።

ሐመረ ፍሬዉ

ጥር 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *