ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ የውጭ ሀይሎች ገንዘባቸውን ያፈሳሉ ፤ ይከስራሉም እኛ ግን ጉዟችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
ተጨማሪም በውስጥ የውይይት በርን ክፍት እንደሚያደርጉየተናገሩ ሲሆን፤ ባንዳ የነበረ ሰው ልብ ገዝቶ ሲመለስ መቀበል ግዴታ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በመሆኑም የግል ስሜትን ወደ ጎን በመተው በኛ ሃሳብ ባይስማሙ እንኳን በኢትዮጵያ ጉዳይ ሲመጣባቸው እና ባንዳ እና ባዳ አንድ ላይ መስራት ሲጀምር ከጦር ሜዳ ለመከላከያ ሰራዊት መረጃ የሚያቀብሉ ተጣቂዎች አሉ ብለዋል፡፡
ወታደር ለህዝቡ ጥቅም እንጂ ከባንዳ ጋር አይደለም የሚቆመዉ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሀና ሰይፉ
ጥር 26/2018 ዓ.ም
