ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህንን ያሉት ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “ኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛውን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርስቲ እየገነባች ነው በሚቀጥለው አንድ ዓመት ውስጥ ስራ ይጀምራል” ብለዋል።
ይህ ዩኒቨርሲቲ አባቶቻችን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ገንብተው ስመጥር እንዳደረጉት ሁሉ ለልጆቻችን ለነገ የተሻለ ዘመን ይዞ ይመጣል ሲሉ ገልጸዋል፡፡፡፡
በኢትዮጵያ ወጣቶችን ለነገ ውድድር ከወዲሁ ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር ከኢትዮጵያ አምስቱ የእድገት ምሰሶዎች አንደኛው ቴክኖሎጂ እንዲሆን በማድረግ ለትውልድ ሲሰራ ቆይቷል ሱሉ አንስተዋል።
ጥር 26/2018 ዓ.ም
