ከለወጡ በፊት ኢትዮጵያ በጣም ብዙ ብድር እንደነበረባትና አበዳሪ ሀገሮች ኢትዮጵያ መክፈል አትችልም አናበድርም ያሉበት ሁኔታ እንደነበረ አንስተዋል።
ለዚህም ህዳሴ ግድባችንን ያለ ምንም እርዳታ ማጠናቀቃችን ምስክር ነዉ ብለዋል፡፡
ብዙዎች ልማት የለም ፣ እድገት የለም ቢሉም እኛ ግን በአፍሪካ አንደኛ የሆነዉን ኮይሻ እየገነባን ነዉ፤ በርካታ ፕሮጀክቶችንም እየሰራን ነዉ ያሉ ሲሆን፤ በአፍሪካ አንደኛ የሆነዉ አየር መንገድም መጀመሩን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ዉስጥ በዚህ ሰአት በሶስት ሺፍት እየተሰራ ዕድገታችን እየጨመረ ነዉ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2018 በጀት ዓመት በ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ይገኛል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥር 26/2018 ዓ.ም
