ፖሊስ መረጃ ለጄፍሪ ኤፕስቲ አሳልፎ ሰጥቷል በሚል በማንዴልሰን ላይ ምርመራ ጀመረ

የለንደን ሜትሮፖሊታን ፖሊስ በቀድሞው የሌበር ፓርቲ ሚኒስትር ፒተር ማንዴልሰን ላይ “በመንግሥት የሥልጣን ዘመን አግባብ ያልሆነ ተግባር መፈጸም” በሚል የወንጀል ምርመራ ጀምሯል።

ይህ የሆነው የቀድሞው ሚኒስትር እና የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የነበሩት ማንዴልሰን፣ የገበያ መረጃን የሚነኩ የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሜሪካዊ የፋይናንስ ባለሙያ እና በጾታዊ ጥቃት ወንጀለኛ ለነበረው ጄፍሪ ኤፕስታይን አሳልፈው ሰጥተዋል በሚል ከተከሰሱ በኋላ ነው።

የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ይፋ ያደረጋቸው ኢሜይሎች እንደሚያሳዩት፣ ሎርድ ማንዴልሰን እ.ኤ.አ. በ2009 በጎርደን ብራውን መንግሥት የንግድ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት መረጃዎችን ለኤፕስታይን ልከዋል። ሎርድ ማንዴልሰን ለቀረበባቸው ጥያቄ ምላሽ ያልሰጡ ቢሆንም፣ “ምንም ዓይነት የወንጀል ድርጊት አልፈጸምኩም እና በገንዘብ ጥቅምም አልተነካካሁም” የሚል አቋም እንዳላቻው ቢቢሲ ተረድቻለሁ ብሉዋል ።

የመንግሥት ቃል አቀባይ “መንግሥት ለፖሊስ አስፈላጊውን ድጋፍ እና እርዳታ ለማድረግ ዝግጁ ነው” ብለዋል። ባለፈው ዓመት ከዩኤስ አምባሳደርነታቸው የተባረሩት ሎርድ ማንዴልሰን፣ ረቡዕ ዕለት ከሎርድስ ምክር ቤት (House of Lords) ለመልቀቅ ማሰባቸውን ለፓርላማው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ሰኞ ዕለት የስኮትላንድ ብሔራዊ ፓርቲ (SNP) እና ሪፎርም ዩኬ የተባሉ ፓርቲዎች ለፖሊስ ጥቆማ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ማክሰኞ ዕለት ደግሞ የእንግሊዝ መንግሥት ሎርድ ማንዴልሰን በሚኒስትርነታቸው ወቅት ለኤፕስታይን የላኳቸውን ኢሜይሎች ከመረመረ በኋላ ጉዳዩን ለፖሊስ መርቶታል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ (No 10) ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ከሆነ፣ ሰነዶቹ “የ2008 የፋይናንስ ቀውስን የሚመለከቱ የገበያ ሚስጥራዊ መረጃዎችን” አካተዋል።

ከ2007 እስከ 2010 ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ጎርደን ብራውን፣ ከማንዴልሰን እና ኤፕስታይን ግንኙነት ጋር የተያያዘ “ጠቃሚ” መረጃ ለፖሊስ ኮሚሽነር ሰር ማርክ ሮውሊ መላካቸውን ገልጸዋል፤ ብራውን ይህ ድርጊት “መንግሥትና አገሪቱ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ቀውስን ለመፍታት በሚታገሉበት ወቅት የተፈጸመ ይቅር የማይባል እና የአገር ክህደት ተግባር ነው” ብለዋል።

የፖሊስ አዛዥ ኤላ ማሪዮት በሰጡት መግለጫ፣ “ከጄፍሪ ኤፕስታይን ጋር የተያያዙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፍርድ ቤት ሰነዶች በአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ይፋ መደረጋቸውን ተከትሎ፣ ፖሊስ ከመንግሥት የቀረበለትን ጥቆማ ጨምሮ በርካታ ሪፖርቶች ደርሰውታል በመሆኑም በ72 ዓመቱ ጎልማሳ እና የቀድሞ የመንግሥት ሚኒስትር ላይ ምርመራ መጀመራችንን አረጋግጣለሁም” ብለዋል።

ሀና ሰይፉ

ጥር 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *