ከአውሮፕላን ነዳጅ በቀር የሌሎች ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል – ንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስቀመጠው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ከትናንት ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ተፈጻሚ ሆኗል።

ከአውሮፕላን ነዳጅ ዉጭ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በጥር በነበረበት ይቀጥላል ተብሏልም፡፡

የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ 136.80 ብር በሊትር እንዲሆን በመንግሥት መወሰኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ጥር 28/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *