በመጪው መጋቢት የሚጀምረው ይህ የሦስት ወር መርሃ-ግብር፤ ከመላው አፍሪካ፣ ከዲያስፖራው እና ከካሪቢያን አገራት ከ1 ሺህ 6መቶ በላይ ማመልከቻዎችን አስተናግዷል፡፡
ገበያን ጨምሮ የመጨረሻዎቹ ስምንት እጩዎች በባንኩ የንግድ ባለሙያዎች እና በቬንቸር ካፒታል ባለሙያዎች በተመራ ጥብቅ የግምገማ ሂደት፣ ቃለ-መጠይቅ እና የንግድ ሃሳብ ማቅረቢያ መድረኮች በኩል ያለፉ ናቸው።
‹‹ገበያ››ባለበት ደረጃ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 2መቶ50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የካፒታል ኢንቨስትመንት ድጋፍ ከአፍሪ-ኤግዚም ባንክ የልማት ፈንድ የማግኘት ዕድል ይኖረዋል።
በተጨማሪም መርሃ-ግብሩ የአማካሪነት አገልግሎት፣ የቴክኒክ ድጋፍ እና የባንኩን ሰፊ የአፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስር የማግኘት ዕድል ይሰጠዋል።
ድርጅቱ እውቅና ያገኘው ለአፍሪካ የንግድ ተቋማት ተስማሚ የሆኑ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዙ ዲጂታል ወኪሎችን በማልማቱ መሆኑን ተዘግቧል።
ጥር 29/2018 ዓ.ም
