መንግስት በቅርቡ ያሻሻለውን አዲሱን የደሞዝ ጭማሬ ከባለፈው አመት ሀምሌ ወር ጀምሮ ለሰራተኞች እየተከፈላቸው መሆኑ ይታወሳል።
ነገር ግን የወላይታ ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6 እና ወላይታ ቴለቪዥን ባንድ አስተዳደር ስር ይሆናሉ ማለትም ድርጅት ይሆናሉ ተብሎ ሲወራ መቆየቱ አይዘነጋም።
ሁለቱም ተቋማት አንድ የሚሆኑበት መንገድ ጥናት ላይ እያለ ባለፈው ሀምሌ ወር ለቴሌቪዥን ሠራተኞች ከሬድዮ ሰራተኞች በልዩ ሁኔታ የትምህርት ዝግጅታቸውን መሠረት ያደረገ የደሞዝ ጭማሪ መደረጉ ተገልጿል።
እንደ አዲስ መንግስት ይጨመራል ያለው ደሞዝ ላላፉት ስድስት ወራት ለሌሎች ሲከፈላቸው ቆይቶ የሬድዮ ቋሚ ሰራተኞች ጠብቁ አንድ ሲሆን ይጨመራል ሲባል እንደነበር ሰራተኞች አንስተዋል።
ትናንት ማታ እስከ ምሽት ሁለት ሰዓት በቆየው ስብሰባ በልዩነት የሬድዮ ሰራተኞች ደሞዝ በአዲስ አሰራር የሁለም በሚባል ደረጃ ከቴሌቪዥን ጋዜጤኞች የ7000 ብር ልዩነት ያለው ደሞዝ ማለትም መነሻ በዜሮ አመት በሬድዮ 9000 ሲሆን፥በቴለቪዥን 16 ሺህ መሆኑን ለሰራተኞች ይፋ አድርገዋል።
ይህ ለምን ሆነ ያሉት የዎጌታ ጋዜጠኞች እና አስተዳደር ሠራተኞች ዛሬ በከፊል ስራ ለማቆም ሙከራ አድረገዋል ነው የተባለው።
ሰራተኞች ለዋና ስራ አስኪያጅ ሞቶሎሚ ጢሞቲዮስ እና ለቦርድ አመራሮች ጥያቄያችንን አድርሱልን እያሉ ይገኛሉ።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 04/2018 ዓ.ም
